Zero One Zero One Tech & Entrepreneurship held an orientation program at Addis Ababa Science and Technology(AASTU)

First-Year students Welcoming and Orientations

Addis Ababa Science & Technology University in collaboration with Zero-One Zero-One Tech Entrepreneurship is warmly welcoming its first-year students and giving orientations.

The Orientation is designed to introduce new students and families to all of the resources and opportunities available to Fresh university students as they start their journey at the university. Students will meet the faculty and staff who are here to support them and begin to build academic and social communities with new classmates from around the country.

The warm reception, as well as the well-organized orientation session, is beautifully done by AASTU and Zero-One Zero-One Tech Entrepreneurship Team. Thank you all for your tremendous help.

Zero-One Zero-One Tech Entrepreneurship your hard work has not gone unnoticed; the university management would like to express their deep gratitude to each and every one of you.

Public and International Relations Directorate

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከዚሮ ዋን ዚሮ ዋን ቴክ ኢንተርፕርነርሽፕ ኃ.የተ. የግ.ተቋም ጋር በመተባበር ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የገለፃ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ-ግብር አዘጋጀ
ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም
ሪፖርተር፡ ያሬድ በቃሉ
ኤዲተር፡ አለምሸት ገ/ወልድ
********************
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲው ለተቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና ስለ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳን ጨምሮ ምክትል ፕሬዚደንቶች ፤ዲኖች እና ከተማሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ተማሪዎች በመጀመሪያው ሳምንት ስለ ዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ መረጃዎችን እንዲያገኙ እና ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በገለፃ ፕሮግራሙ ላይ ዶ/ር ደረጀ እንግዳ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት በቅድሚያ እንኳን ዳህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በዜሮ ሳምንት መርሃ ግብር ዩኒቨርሲቲው ያለውን የላብራቶሪ፤የትምህርት አይነቶችን እንዲሁም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከአጠናቀቁ በኋላ በምን አይነት የስራ ዘርፎች ላይ መሰማራት እንደሚችሉ መረጃዎችን የሚያገኙበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ደረጀ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው በአካዳሚክ ብቻ ልቆ መገኘት ሳይሆን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎት እንዲኖራቸው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ባሉ ክበባትና የፈጠራ ማበልፀጊያ ማዕከላት ውስጥ በመሳተፍ አዳዲስ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ አሳስበዋል፡፡ከሁሉም በላይ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አለም ዓቀፋዊ የሆኑ ተመራቂዎች እንዲሆኑ የተግባቦት ፤የኢንተርፕርነርሽፕ ክህሎት ሊያዳብሩ ይገባል ሲሉ ጨምረው አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታረቀኝ ብርሃኑ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የሚታወቅበትን ሰላም፤ፍቅር፤አንድነት እና ህብረት በማስቀጠል ምርጥ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ደበበ በበኩላቸው ተማሪዎች የዳበረ አመለካከት ኖሯቸው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉትን መልካም ዕደሎች በመጠቀም የፈጠራ እና ምርምር ክህሎትን ማሳደግ እንደሚገባቸው መክረዋል፡፡ ዶ/ር አብረሃም አያይዘውም ተማሪዎች በማህበረሰብ አገልግሎት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡
 በተመሳሳይ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ከማል ኢብራሂም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በእርሳቸው ዘርፍ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
 ከተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን ተስፋየ አዲስ ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉ ተማሪዎች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውና ምን ማድረግ እንዴሌለባቸው ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በመርሃግብሩ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ልምድ እና ተሞክሯቸውን ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አካፍለዋል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ከተማሪዎች ውጤት እና ፕሮግራም ጋር በተገናኘ ገለፃ ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ፅ/ቤት ዳይሬክተር ዶ/ር ፀጋዬ በለገ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከምዝገባ ፤ከኮርስ እና ከውጤት ጋር በተያያዘ መከተል የሚገባቸውን ህጋዊ አካሄዶች ለተማሪዎች ገልፀዋል፡፡
ይህ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የገለፃ ፕሮግራም እንዲሳካ ለሰሩ የዩኒቨርሲቲው የስራ ክፍሎች እና ኃላፊዎች እንዲሁም ለዚሮ ዋን ዚሮ ዋን ቴክ ኢንተርፕርነርሽፕ ኃ.የተ. የግ.ተቋም ሰራተኞች የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ተመሳሳይ የገለፃ እና የጉብኝት ፕሮግራሞች ነገ እና ከነገ በስተያ የሚቀርቡ በመሆኑ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው አዲስ ተማሪዎች መገኘትና መሳተፍ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት